Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የወገን ጦር ካሳጊታን መቆጣጠሩን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግንባር ባስተላለፉት መልዕክት የወገን ጦር በከፍተኛ ሞራልና ወኔ እየተዋጋ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ጠላት የያዛቸውን ቦታዎች እያስለቀቀ መሆኑን ጠቅሰው፥ ጠላት የወገንን ጦር የመገዳደር አቅም እንደሌለውም ነው የገለጹት።
በጠላት እጅ ስር የነበሩ ቦታዎችን መከላከያ ሰራዊቱ እየተቆጣጠረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ የወገን ጦር ካሳጊታን መቆጣጠሩን ጠቁመው፥ ቡርቃ እና ጭፍራን ዛሬ እንደሚቆጣጠርም አስታውቀዋል።
ምሽግ ውስጥ አድረን አገራችንን ማሻገር ነው የምንፈልገው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የኢትዮጵያ ነጻነት እስኪረጋገጥ ወደ ኋላ አንልም፣ የምንፈልገው እኛ ሞተን የምትቆም ኢትዮጵያን ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም የህዝብ ድጋፍ ያለን በመሆኑ በድል እንደምንወጣው እርግጠኞች ነን ብለዋል ባስተላለፉት መልዕክት።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.