Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጀርመን መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጀርመን መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ ውይይት አካሄደዋል።

ውይይታቸውም በኮቪድ 19ን በመከላከል እና ስርጭቱን በመግታት ላይ አተኩሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በውይይቱም፥ በዚህ ፈታኝ ወቅት ጀርመን ከኢትዮጵያ ጎን ለመቆም ያላትን ቁርጠኝነት እና አጋርነት አድንቀዋል።

ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ ስለለገሰችው የኮቪድ 19 መመርመሪያ ግብዓትና መገልገያ ቁሳቁሶችም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ታላቁን የህዳሴ ግድብ አስመልከቶ ለሁሉም አካላት የሚያመች ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፉም በውይይታቸው  ገልፀዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.