Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ1፣2012 ( ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ አደረገ፡፡

የኮረና ቫይረስ ማህበራዊና ሰብአዊ ቀውስ ከማስከተሉ በተጨማሪ ከባድ የኢኮኖሚ ችግር እያስከተለ ነው ያለው ጠቅላይ አቃቤ ህግ፥ በኢኮኖሚው መዳከም ምክንያት ግብር ከፋዬችና በአጠቃላይ የንግድ ማህበረሰቡ ስራቸውን ለማቆም ስለሚገደዱ ፣ በርካታ ዜጎች ከስራ ስለሚያፈናቅሉ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር የሚዳርግ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ያለባቸውን ውዝፍ የግብር፣ የታክስ እና ቀረጥ ነፃ በማቃለል ለታክስ ክፍያ ሊያውሉት ይገባ የነበረውን ገንዘብ ለስራ ማስኬጃ በማዋል በንግድ ስራ ውስጥ እንዲቀጥሉ ለማድረግ እንዲችሉ መንግስት የታክስ ምህረት ማድረጉን አስታውሷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መንግስት የኢኮኖሚ ጫናውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ኪሳራን ከማሸጋገር ጀምሮ የተለያዩ ተጨማሪ ውሳኔዎችን መወሰኑን ነው ያስታወቀው፡፡

በዚሁ መሰረት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግም በመንግስት የተሰጡትን የተለያዩ ውሳኔዎችን መነሻ በማድረግ የወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ ዝርዝር የውሳኔ መመሪያ ( exit strategy ) በማዘጋጀት ነጋዴውን የሚመለከቱ የወንጀል የምርመራ መዛግብቶች እና በፍርድ ቤት በመደበኛና በይግባኝ በክርክር ላይ የሚገኙ ያለደረሰኝ ግብይት፣ ታክስ ስወራ እና አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ክስ እንዲሁም በኮንትሮባንድ ወንጀል በምርመራ ላይ ያሉና ክስ የተመሰረተባቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ክሳቸው እንድቋረጥ መደረጉን ገልጿል፡፡

በቀጣይ የሚቋረጡ መዛግብቶች እንዳሉ ሆኖ በመመሪያው መሰረት እስካሁን የተቋረጡ መዛግብት ዝርዝርን ይፋ አድርጓል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.