Fana: At a Speed of Life!

ጠፍቶ የነበረው የ18ኛው ክፍለ ዘመን ዘውድ ነገ ለጨለቆት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ይመለሳል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ ከኔዘርላንድስ የተመለሰው የ18ኛው ክፍለ ዘመን ዘውድ በነገው እለት ለትግራይ ክልል ጨለቆት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ተመላሽ ይደረጋል።

በዕለቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት በብሔራዊ ሙዚየም ቅጥር ግቢ የርክክብ ሥነ ሥርዓትና ሽኝት እንደሚካሄድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኔዘርላንድስ የውጭ ንግድ እና የልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ ዘውዱን ከሳምንት በፊት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማስረከባቸው ይታወሳል።

ከ19 85 ዓ.ም ጀምሮ ጠፍቶ የነበረው ዘውድ ባለፈው አመት ጥቅምት ወር ላይ በኔዘርላንድስ ሮተርዳም ከተማ መገኘቱም የሚታወስ ነው።

ዘውዱ በኔዘርላንድስ መንግስት እና በትውልደ ኢትዮጵያዊው በአቶ ሲራክ አስፋው ትብብር ነበር ወደ ሀገር ቤት የተመለሰው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.