Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ለምርጫ ያልተመዘገቡ መራጮች ቀሪውን የምርጫ መመዝገቢያ ጊዜ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለምርጫ ያልተመዘገቡ መራጮች ቀሪውን የምርጫ መመዝገቢያ ጊዜ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት ሳምንታት በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገባችሁ ዜጎች ሁሉ መልካም አድርጋችኋል ብለዋል፡፡
በዘንድሮው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ሰዎችም ቁጥር ከ5ኛው ብሔራዊ ምርጫ ተመዝጋቢዎች ቁጥር እየበለጠ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
ምዝገባው ሊጠናቀቅ አሁንም ጥቂት ቀናት ይቀራሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልተመዘቡ ሰዎች ነገን የመወሰን መብታቸውን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.