Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ከተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበጃፓን ቶኪዮ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ የሚደረጉ ዝግጅቶችን ለማስተባበር ከተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ ወቅት ኮሚቴው ለቶኪዮ ኦሊምፒክ እያደረገ ያለውን ዝግጅት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በውድድሩ ከተሳትፎ ባለፈ አትሌቶች በድል እንዲመለሱ የማገዝ አላማ እንዳለው መግለጹን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2020 በሚካሄደው የጃፓን ቶኪዮ 32ኛው የኦሎምፒክ ውድድር በአትሌቲክስ፣ በቦክስ፣ በእግር ኳስ፣ በብስክሌት፣ በውሃ ዋና፣ በካራቴ፣ በወርልድ ቴኳንዶና ዒላማ ተኩስ ስፖርቶች ለመሳተፍ እቅድ ይዛለች።

በተደረጉ ግምገማዎች ቅርጫት ኳስና እጅ ኳስ ውድድሮች ከሌሎቹ ከታቀዱት 8 ስፖርቶች በተጨማሪ በእቅድ ውስጥ ለማካተት ሀሳብ እንዳለ ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ስፖርቶች በቶኪዮ ኦሊምፒክ ውድድር አገራቸውን ወክለው መሳተፍ በሚያስችላቸው የማጣሪያ ውድድሮች ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.