Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ ጉዳይ ከአገር ሉዓላዊነት ጋር የተያያዘ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአማራ ክልል በቆጋ መስኖ የሚገኘውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተገኝተዋል፡፡

በበጋው በአማራ ክልል ወደ 13 ሺ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በመስኖ ስንዴ እየለማ ይገኛል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆጋ መስኖ እየለማ ያለ የአቮካዶ ማሳንም ጎብኝተዋል።

በአማራ ክልል 7500 ሄክታር መሬት ላይ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ አቮካዶ በክላስተር እየለማ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት አካባቢው ለኢትዮጵያ የግብርና ምርት የዕድገትና ለውጥ ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ ጉዳይ ከአገር ሉዓላዊነት ጋር የተያያዘ መሆኑን አርሶ አደሩ ጠንክሮ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከውጭ ሀገራት የሚገባውን ስንዴን ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የአቦካዶ ኤክስፖርት በጥቂት ዓመታት ውስጥ የቡና ኤክስፖርት ጋር እንደሚስተካከል አንስተዋል፡፡

በአላዘር ታደለ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.