Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ቢላሉል ሐበሺ ሙዚየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ቢላሉል ሐበሺ ሙዚየምን ጎብኝተዋል።

ሙዚየሙ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ታሪክ እና ቅርስ የሚያስተዋውቅ ነው።

በውስጡም እስልምና ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ያሉ ታሪኮች ተደራጅተው ተቀምጠዋል ።

ከተጻፉ ረዥም አመታትን ያስቆጠሩ ቁርዓን እና ኪታቦችም በሙዚየሙ አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ታሪክ የማስተዋወቁ ስራ በስፋት እንዲሰራ አሳስበዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ1442ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ቀን ሙዚየሙን መጎብኘታቸው ትልቅ ደስታ እንደፈጠረባቸው የቢላሉል ሐበሺ የልማት እና መረዳጃ እድር መስራቾች ተናግረዋል ።

እድሩ ከሙዚየም ግንባታው ባለፈ ከ10 ሺ በላይ ድጋፍ የሚሹ ልጆችን አስተምሯል ።

ቤተ መጽሐፍ ፣ ሁለገብ አዳራሽ ፣ የጥናትና ምርምር ማዕከል አቋቁሞም አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ።

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.