Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከካናዳ አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከካናዳ አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጀስቲን ትሩዶ ጋር በሀገራዊ እና ቀጣናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ነው የገለጹት።

ካናዳ ለኢትዮጵያ የዘወትር አጋር ሆና ቆይታለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ግንኙነታችን ላይ ተመሥርተን ትብብራችንን እናጠናክራለን ብለዋል።

እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስላደረጉት ገንቢ ውይይት ጠቅላይ ጀስቲን ትሩዶን  አመሰግነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.