Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ‘የመደመር መንገድ’ መጽሐፍ ነገ ገበያ ላይ እንደሚውል አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ‘የመደመር መንገድ’ የተሰኘው መጽሐፍ ነገ ገበያ ላይ እንደሚውል አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጽሐፉ፥ የለውጡን ፈለግ እና መደመር ያለፈበትን መንገድ ወደ ኋላና ወደ ፊት፣ መለስ ቀለስ እያለ እንደሚዳስስ ተናግረዋል፡፡
በብዙ ውጣ ውረዶች አልፎ ዛሬ ላይ የደረሰውን ለውጥ የወለዱ አስተሳሰቦች ምን እንደሆኑ፣ ከጥንስሱ ጀምሮ የሪፎርም ጉዞው ምን እንደሚመስል፣ በሂደት የተፈጠሩ መልካምና ፈታኝ አጋጣሚዎች እንዲሁም ተጓዳኝ ታሪኮችን ይዟልም ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እጽፋቸዋለሁ ብለው ሳይፅፉ ለረጅም ዘመናት የቆዩ ትዝታቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር የተጋሯቸው ወዳጃዊ ሐሳቦች ጭምር በመፅሃፉ እንደተካተቱ ገልፀዋል።
በብዙ ጉዳዮች ላይ የተሻለ ግንዛቤ ይሰጣል የሚል እምነት አለኝም ብለዋል።
ቀደም ሲል ለወጣው መጽሐፍ እንደ ተከታይና አስረጂ ሆኖ እንዲያገለግል ዘርዘርና ሰፋ ብሎ፣ ከመጠነኛ የአጻጻፍ ቅርጽ ለውጥ ጋር የተሰናዳ መጽሐፍ ነው።
መጽሐፉ ከሁለት ዓመት በላይ የሆነ ጊዜ እንደወሰደ ገልፀው የተጀመረበት ወቅት ከዚያኛው የመደመር መጽሐፍ ቢቀድም እንጂ አይዘገይም ብለዋል።
መፅሃፉም በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ተሰናድቶ የኅትመት ሥራው የተጠናቀቀ ሲሆን በነገው እለትም ለአንባቢ ይደርሳል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.