Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከትናንት ጀምሮ በግንባር አመራር እየሰጡ ነው-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢትዮጵያ የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ መሪዎችና ህዝቡ የሽብር ቡድኑን ህወሓት ለመደምሰስ በግንባር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡
 
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ነው።
 
በመግለጫቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከትናንት ጀምሮ በግንባር አመራር እየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።
 
ሌሎች አመራሮችም የህልውና ዘመቻውን በመቀላቀል ወደ ግንባር መዝመታቸውን ነው የገለጹት፡፡
 
መደበኛ ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እየተመራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመታቸው በርካቶችን ያነቃቃና በርካቶች እንዲከተሏቸው አድርጓልም ብለዋል ዶክተር ለገሰ።
 
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት የአመራር ብቃታቸውንና የቆየ የአይበገሬነት ታሪክን ያሳያልም ነው ያሉት።
 
ጦርነቱን በጠመንጃ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ ስለሆነ በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች መስራት የሁሉም ዜጎች ሃላፊነት መሆኑን ጠቁመዋል።
 
በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ጦርነት በአንድ በኩል ጥምር ሽብር ቡድኖች፣ በሌላ በኩል የኢትዮጵያን ልዕልናንበማይፈልጉና ወደ ኋላ ለመጎተት በተነሱ ሃይሎች የተከፈተ እንደሆነም ሚኒስትሩ አንስተዋል።
 
ይህንን ለመመከትም ዜጎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ መገናኛ ብዙሃን፣ ዳያስፖራው ሃገርን ለመታደግ የሚደረገውን ትግል እንዲደግፉ ጠይቀዋል።
 
የውጪ መገናኛ ብዙሃን በግራጫ ውሸታቸው ቀጥለውበታል ያሉት ዶክተር ለገሰ÷ ከበሬ ወለደ ዜና እስከ ባለስልጣናት ያላሏቸውን እስከመዘገብ መድረሳቸውን ጠቅሰዋል።
 
በአፈወርቅ እያዩ እና በርናባስ ተስፋዬ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.