Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ፡፡

ውይይቱ በዋናነት በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስራኤል ከተባበሩት ዓረብ ኢሚቴቶች እና ባህሬን ጋር ለደረሰችው ታሪካዊ ስምምነት ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የተደረሰው ታሪካዊ ስምምነት በትውልድ ያለውን ፋይዳ በተመለከተም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው ወቅት ገልጸውላቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ እስራኤል በሚመለሱበት ሁኔታና ተያያዥ ጉዳዮች ላይም መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሃገራቱ በግብርናው ዘርፍ በሚኖራቸው ትብብርና እስራኤል ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከር በምትችልበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል፡፡

እንዲሁም ሃገራቱ ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር በሚችሉበት አግባብ ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.