Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ ኮቪድ19ኝን የመከላከል ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተግባራዊ ባደረገ መልኩ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል በሚደረገው ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምንም ዓይነት የሰላም እና የጸጥታ ችግር እንዳይከሰትና ችግር ቢከሰት ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍ ተቋማቱ ባላቸው ዝግጁነት ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የዕውቀት እና የፈጠራ ማዕከላት እንደ መሆናቸው መጠን አመራሮች ለትምህርት እንዲሁም ለቱሪዝም የሚሆን ነባራዊ ሁኔታ እንዲያመቻቹ ቀጣይ አቅጣጫ መቀመጡንም አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.