Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው የሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና በአፍሪካ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ሲሪል ራማፎሳ የአፍሪካ ህብረትን የወቅቱ ሊቀመንበርነት ተረክበው መንቀሳቀስ ከጀመሩ አንስቶ ፤ የአፍሪካ ጉዳዮች በአፍሪካውያን እንዲፈቱ እያደረጉት ላለው ጥረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለፕሬዚዳንቱ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.