Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የብሔራዊ ስታዲየም የግንባታ ሂደትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ስታድየም ግንባታን ዛሬ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
አጠቃላይ የስታዲየሙ ግንባታ ሂደት ያለበት ሁኔታ እና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ በአማካሪ ድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በዶክተር ኢንጅነር መሰለ ሀይሌ እና የግንባታውን ሂደት በሚከታተሉት በአቶ አስመራ ግዛው ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም መንግስት ስታዲየሙ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ያጋጠሙ ችግሮችን እንደሚፈታ ገልፀው÷ ግንባታው በአጭር ግዜ ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ እና ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በጉብኝቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የኤም ኤች ኢንጂነርግ ማኔጅንግ ዳይሬክር ዶክተር መሰለ ሀይሌ እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የኮንትራክተሩ ባለሙያዎች መገኘታቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.