Fana: At a Speed of Life!

ጣሊያን ድንበሮቿን ዳግም ክፍት አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን ዘግታቸው የነበሩ ድንበሮቿን ዳግም ክፍት ማድረጓን አስታወቀች።

ይህን ተከትሎም ከተለያዩ ሃገራት ወደ ጣሊያን መግባት የሚፈልጉ መንገደኞች ያለ ለይቶ ማቆያ ቀጥታ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል ነው የተባለው።

የአሁኑ እርምጃ ለቀጣዩ የፈረንጆች የበጋ ወቅት ጎብኚዎች ወደ ሃገሪቱ እንዲገቡ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

ቱሪዝም ከሃገሪቱ ዋነኛ የገቢ ምንጮች ቀዳሚው እንደሆነ ይነገራል።

ከድንበር መከፈቱ ባለፈም የሃገር ውስጥ በረራዎች በሁሉም አካባቢዎች እንዲጀመሩ መንግስት ፈቅዷል።

ጣሊያን በኮቪድ19 ምክንያት ከአውሮፓ ሃገራት ከፍተኛውን ጉዳት አስተናግዳለች።

በሃገሪቱ ወረርሽኙ ከገባ ወዲህ እስካሁን ከ33 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.