Fana: At a Speed of Life!

ጣና ፎረም ለአፍሪካ ጉዳዮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ከማምጣት ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ አለው-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጣና ፎረም በአፍሪካ ውስጥ ላሉ የሰላምና የደህንነት ጉዳዮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ከማምጣት ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

በአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚመክረው ጣና ፎረም ለ9ኛ ጊዜ “ለአፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ልማት የፓን አፍሪካ እሳቤን ማጠናከር” የሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በቪዲዮ ኮንፈረንስ በታገዛው የዘንድሮው የጣና ፎረም ላይም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመትን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በንግግራቸውም፦ ፎረሙ በአፍሪካ ውስጥ ላሉ የሰላምና የደህንነት ጉዳዮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ከማምጣት ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

ፕሬዝደንቷ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ዝውውር ቀጣና ስምምነት ፓን-አፍሪካኒዝምን በማነቃቃትና በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም እና እድገትን ከማስገኘት አንጻር ያለዉን ሚና የጎላ መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል።

“በከባድ ጊዜ ውስጥ እያለፍን እንገኛለን” ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በጤና እና በምጣኔ ሀብት ላይ ያስከተለው አሉታዊ ተፅዕኖ አለም እቀፍ ምጣኔ ሀብትን መጉዳቱንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ችግር ለመውጣትና ለመሻሻል በሚደረግ እንቅስቃሴ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ዝውውር ቀጣና ስምምነት ያለዉን አዎንታዊ ተጽዕኖ መገንዘብ ያስፈልጋልም ብለዋል።

ወረርሽኙ ያስከተላቸዉ ሁለገብ ችግሮች ከምንግዜውም በበለጠ በአፍሪካ አገራት መካከል የሚደረግ ንግድ ያለዉን ጠቀሜታ አሳይቷል ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.