Fana: At a Speed of Life!

ጥረት ኮርፖሬት ለአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎች ከ20 ሚሊየን ብር በላይ እና የአይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ጥረት ኮርፖሬት በሃገር ህልውና ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከት ለተሰለፈው የአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎች ከ20 ሚሊየን ብር በላይ እና የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ከገንዘብ እና አይነት ድጋፉ በተጨማሪ በግንባር የመሰለፍና የደም ልገሳ ድጋፎችም በኮርፖሬቱ ሰራተኞችና አመራሮች በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

ድጋፉ የተሰበሰበው ከ4 ሺህ 700 በላይ የጥረት ኮርፖሬትና የኩባንያ እንዲሁም የፕሮጀክት ሰራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን በመለገሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጥሬ ገንዘብና በዓይነት የተደረገው ድጋፍ አጠቃላይ መጠኑ ከ20 ሚሊየን ብር እንደሚልቅ የአሰባሳቢው ግብረ ኃይል ኮሚቴ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም የጥረት ኮርፖሬትና የኩባንያ ሰራተኞችን በበጎ ፈቃድ በማስተባበር ከ1 ሺህ በላይ ከረጢት ደም ለማሰባሰብ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመመከት ወደ ግንባር የዘመቱ ሰራተኞች መኖራቸውንና በቀጣይም ለመዝመት ፍላጎት ያላቸው የጥረት ሰራተኞች በምዝገባ ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡

በተመሳሳይ ‘‘የህልውና ዘመቻውን ከመመከት ጎን ለጎን ክልላችንን እናለብሳለን’’ በሚል መሪ ቃል ከ50 ሺህ በላይ ችግኞችን የመትከል ሥራም እየተከናወነ እንደሚገኝ ከኮርፖሬቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የጥረት ኮርፖሬትና ኩባንያ ሰራተኞች ለልዩ ኃይሉ ድጋፍ ሲያደርጉ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን÷ በቀጣይም ግንባር ድረስ በመሳተፍ ግዴታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.