Fana: At a Speed of Life!

ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ተግባር የሚያወግዝ ሰልፍ በሲዳማ ክልል ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ተግባር የሚያወግዝ ሰልፍ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል።
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሚሊኒየም አደባባይ በተካሄደው ሰልፍ ላይም የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተውጣጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት፥ በሀገር ክህደት የሚታወቁት እነዝህ አሸባሪዎች አለኝታችን በሆነው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሱት ጥቃትና ግፍ ከህሊና ቢስነት የመነጨ ነው ብለዋል።
የክልሉ ህዝብ ላሳየው የደጀንነት ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው፤ እንደ ከዚህቀደሙ የክልሉ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የሲዳማ ክልል ነዋሪዎችም ከሀዲውን ቡድን በሚያያወገዙ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በሚደግፉ በተለያዩ መፈክሮች ታጅበው ነው በሰልፉ ላይ የተገኙት።
ከመፈክሮቹ መካከልም “በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ከሃዲው ጁንታ የህወሃት ቡድን የወሰደውን እርምጃ እንቃወማለን፣ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ሆነን የሚጠበቅብንን ድጋፍ ሁሉ እናደርለን” የሚሉ ይገኙበታል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት በፅንፈኛው ጁንታ ላይ እየወሰደ ያለውን ህግን የማስከበር እርምጃ በሁሉም መንገድ እንደሚደግፉም የሰልፉ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በህዝቦች መስዋዕትነት የተገነባች በመሆኗ በእናት ጡት ነካሽ ጁንታዎች አትፈርስም ያሉት የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም የሚጠበቅብንን ሁሉ ድጋፍ እናደርጋለንም ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.