Fana: At a Speed of Life!

ፆምና የጤና ጠቀሜታው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የዐቢይን ፆም ከጀመሩ ከአንድ ወር በላይ ያስቆጠሩ ሲሆን የእስልምና እምነት ተከታዮችም በዛሬው ዕለት የረመዳን ፆምን ጀምረዋል።

በሁለቱም እምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው የጾም ወቅቶች ጋር ተያይዞም የፆም ጠቀሜታዎች ለማንሳት ወደናል።

ፆም በበርካታ ህዝቦች የሚከወን እና በተለይም በሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ላይ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ተግባር ነው።

ከዚህ ቀደም በኒው ሜዲካል ጆርናል መጽሄት ላይ የወጣው የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በቀን ከ16 እስከ 18 ሰዓት ምግብ ሳይመገቡ ማሳለፍ የተለያዩ የጤና በረከቶችን ያስገኛል።

በመሆኑ ከፆም የሚገኙ የጤና ጠቀሜታዎች ምንድ ናቸው

  1. በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር፣

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጾም በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በተሻለ መንገድ ለመቆጣጠርና በተለይም የስኳር በሽታ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ጠቃሚ መሆኑ ነው የተጠቆመው።

  1. እብጠትን በመከላከል ሰዎች ጤናማ እንዲሆኑ ያስችላል

ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጡ ጥናቶች በጾም ወቅት ሰውነት የሚያገኘው የካሎሪ መጠን ከመቀነሱ ጋር ተያይዞ ሰውነት ላይ የሚከሰት እብጠት እንደሚቀንስ ያሳያሉ።

በአንድ ጥናት ላይ የተሳተፉ 50 ሰዎች ለአንድ ወር እንዲፆሙ የተደረገ ሲሆን በዚህም ከፍ ባለሁኔታ የእብጠት መጠን እንደቀነሰላቸው ተጠቁሟል።

ሌላኛው ጥናትም ሰዎች ለ12 ሰዓታት ሲፆሙ ተመሳሳይ ውጤት እንደተመለከቱ ተነግሯል።

  1. የደም ግፊትን እና የኮሌስትሮል መጠንን ለመከላከል

ለከፍተኛ ክብደት የተጋለጡ ሰዎች በተደጋጋሚ እንዲፆሙ ተደርጎ የሰውነት ክብደታቸው መቀነሱ ተጠቅሷል።

የሰውነት ክብደታቸው መቀነሱ ደግሞ የደም ግፊታቸውና የኮሌስትሮል መጠናቸው እንዲቀንስ ረድቷቸዋል፤ ይህ ደግሞ ከልክ በላይ በሆነ ውፍረት ሊከሰት የሚችለው የልብ ጤንነት ችግር መቅረፍ ያስችላልም ነው የተባለው።

ፆም የአዕምሮ የመስራት አቅምን ያፋጥናል፣ ከነርቭ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን ይከላከላል፣ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፣ ካንሰርን ለመከላከል እና ለምግብ መፈጨትና ለስርአት ምግብ መንሸራሸርን ለማፋጠን ይረዳል።

እንዲሁም  ክብደት ለመቀነስ እና አጥንትን ለማጠናከር ወሳኝ የሆነውን ሆርሞን እድገት ለመጨመር እንደሚረዳም ነው የተጠቆመው።

ምንጭ፦ healthline.com

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.