Fana: At a Speed of Life!

ፆምና የጤና ጠቀሜታው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፆም በበርካታ ህዝቦች የሚከወን እና በተለይም በሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ላይ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ተግባር ነው።

ከዚህ ቀደም በኒው ሜዲካል ጆርናል መጽሄት ላይ የወጣው የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በቀን ከ16 እስከ 18 ሰዓት ምግብ ሳይመገቡ ማሳለፍ የተለያዩ የጤና በረከቶችን ያስገኛል።

በመሆኑ ከፆም የሚገኙ የጤና ጠቀሜታዎች ምንድ ናቸው

1. በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር፣

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጾም በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በተሻለ መንገድ ለመቆጣጠርና በተለይም የስኳር በሽታ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ጠቃሚ መሆኑ ነው የተጠቆመው።

2. እብጠትን በመከላከል ሰዎች ጤናማ እንዲሆኑ ያስችላል

ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጡ ጥናቶች በጾም ወቅት ሰውነት የሚያገኘው የካሎሪ መጠን ከመቀነሱ ጋር ተያይዞ ሰውነት ላይ የሚከሰት እብጠት እንደሚቀንስ ያሳያሉ።

በአንድ ጥናት ላይ የተሳተፉ 50 ሰዎች ለአንድ ወር እንዲፆሙ የተደረገ ሲሆን በዚህም ከፍ ባለሁኔታ የእብጠት መጠን እንደቀነሰላቸው ተጠቁሟል።

ሌላኛው ጥናትም ሰዎች ለ12 ሰዓታት ሲፆሙ ተመሳሳይ ውጤት እንደተመለከቱ ተነግሯል።

3. የደም ግፊትን እና የኮሌስትሮል መጠንን ለመከላከል

በተለያዩ ጥናቶች ለከፍተኛ ክብደት የተጋለጡ ሰዎች በተደጋጋሚ እንዲፆሙ ተደርጎ የሰውነት ክብደታቸው መቀነሱ ተጠቅሷል።

የሰውነት ክብደታቸው መቀነሱ ደግሞ የደም ግፊታቸውና የኮሌስትሮል መጠናቸው እንዲቀንስ ረድቷቸዋል፤ ይህ ደግሞ ከልክ በላይ በሆነ ውፍረት ሊከሰት የሚችለው የልብ ጤንነት ችግር መቅረፍ ያስችላልም ነው የተባለው።

ፆም የአዕምሮ የመስራት አቅምን ያፋጥናል፣ ከነርቭ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን ይከላከላል፣ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፣ ካንሰርን ለመከላከል እና ሜታቦሊዝምን ለ ማፋጠን ይረዳል።

እንዲሁም  ክብደት ለመቀነስ እና አጥንትን ለማጠናከር ወሳኝ የሆነውን ሆርሞን እድገት ለመጨመር እንደሚረዳም ነው የተጠቆመው።

ምንጭ፦ healthline.com

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.