Fana: At a Speed of Life!

ፈረሰኞቹ በቻምፒየንስ ሊጉ ቅድመ ማጣሪያ ከሱዳኑ አልሂላል ጋር ይጫወታሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሱዳኑ አልሂላል ጋር እንደሚያደርግ ታውቋል።

ዛሬ ካይሮ ላይ በወጣው የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ እጣ አወጣጥ ፕሮግራም መሠረት ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሜዳቸው ያደርጋሉ።

ቡድኑ በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ጨዋታው ከደቡብ ሱዳን ከዛለን እና ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል።

በተያያዘ የ2014 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግን በሁለተኝነት ያጠናቀቀው የፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከቡሩንዲው ቡማሙሩ ጋር እንደሚያደርጉ ታውቋል።

ዓፄዎቹ በቅድመ ማጣሪያው ካሸነፉ ቀጣይ ጨዋታቸውን ከቱኒዚያው ሴፋክሲን ጋር ያደርጋሉ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.