Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ለጋሲዮን ጨፌ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው የስፖርት ሜዳ በ25 ሚሊየን ብር ለመገንባት ርክክብ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፈረንሳይ ለጋሲዮን ጨፌ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው የስፖርት ሜዳ ግንባታን በ4 ወራት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ የሳይት ርክክብ ተደረገ ።
ለግንባታው 25 ሚሊየን በጀት መያዙን የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ለወጣቶች የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎችን በማደስ እና የማሻሻያ ግንባታ በማድረግ ልዩ ትኩረት ለመስጠት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡
በዛሬው ዕለትም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የፈረንሳይ አካባቢ የጨፌ ሜዳ ግንባታ ውብኮን ኮንስትራክሽን የተባለ ስራ ተቋራጭ አማካኝነት በአራት ወራት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ የሳይት ርክክብ ተካሂዷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ኮንስትራክሽን ቢሮ ተወካዮች ፣የየካ ክፍለ ከተማ ስፖርት ፅህፈት ቤት በተገኙበት ለውብኮን ኮንስትራክሽን እና ዘውዱ ተስፋዬ የሳይት ርክክብ ተካሂዷል።
ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ በፍጥነት እና በጥራት አጠናቆ ለስፖርት ቤተሰቡና ለወጣቱ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሜዳው አንድ ደረጃውን የጠበቀ እግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ፣ ሁለት የፉትሳል ሜዳዎች ፣የመሮጫ ትራክ ፣ የተመልካች መቀመጫ፣ዙሪያ የሽቦ አጥር፣ሻወር ቤት ፣የቲኬት ቢሮ እና የልብስ መቀየሪያ ክፍሎች የሚያካትት መሆኑ ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.