Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ በሰሜን አፍሪካ የአል ቃይዳን መሪ መግደሏን አስታወቀች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ በሰሜን አፍሪካ የአል ቃይዳን መሪ መግደሏን አስታወቀች።

የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ፍሎረንስ ፓርሊ በማሊ በተካሄደ ዘመቻ በሰሜን አፍሪካ የቡድኑ መሪ የሆነው አብድልማሌክ ድሮክዴል መገደሉን ተናግረዋል።

በዘመቻው የእርሱ የቅርብ አጋር የሆኑ የቡድኑ አባላት መገደላቸውንም ነው የተናገሩት።

ግለሰቡ በሰሜን አፍሪካ በተለይም በሳህል ቀጠና አካባቢ ከቡድኑ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ታጣቂ ቡድኖች የማደራጀትና የመምራት ሃላፊነትን ይወጣ ነበር ተብሏል።

ቡርኪና ፋሶን ጨምሮ በአንዳንድ ሃገራት የደረሱ ጥቃቶችን ማቀናበሩንም መረጃወች ያመላክታሉ።

ወደ ሰሜን አፍሪካ ከመምጣቱ አስቀድሞ በአፍጋኒስታን እና በኢራቅ ይንቀሳቀስ ነበርም ነው የተባለው።

በፈረንጆቹ 2007 በአልጀሪያ በደረሰውና 22 ሰዎችን ለህልፈት በዳረገው የሽብር ጥቃት በሃገሪቱ ፍርድ ቤት በሌለበት የሞት ፍርድ ተበይኖበት ነበር።

ፈረንሳይ በወሩ አጋማሽ አካባቢ በማሊ ይንቀሳቀስ የነበረን የአይ ኤስ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ መያዟን መግለጿ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.