Fana: At a Speed of Life!

ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችና ተቋማት በጥምቀት በዓል ድሮን መጠቀም እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመላከል ከሚመለከተው አካል ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ድሮን ማብረር ወይንም ማንቀሳቀስ እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታዉቋል።

ኮሚሽኑ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ሁሉም የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ከከተራ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በድምቀት የሚከበረዉ የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቂ ዝግጅት አድርገዋል።

ከፀጥታ አጠባበቅ ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከልም የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።

ከተገቢው አካል ፈቃድ ሳይኖራቸው ድሮኖችንም እንዳያበሩ ወይንም እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ድሮንን ለተለያዩ አገልግሎቶች ለማዋልም ህጋዊ ስልጣን ካለዉ አካል ፈቃድ ማውጣት እንደሚቻል ተገልጿል።

በዚህ አጋጣሚ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የጥምቀት በዓል እንዲሆን ምኞቱን እየገለፀ ሕብረተሰቡ ከበዓሉ አከባበር ጋር ተያይዞ ሰላምን የሚያደፈርሱ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለጸጥታ አካላት የተለመደ ጥቆማውን እንዲሰጥ ጠይቋል።

ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመከላከል ከሚመለከተው አካል ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ድሮን ማብረር ወይንም ማንቀሳቀስ እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታዉቋል።

ኮሚሽኑ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ሁሉም የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ከከተራ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በድምቀት የሚከበረዉ የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቂ ዝግጅት አድርገዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.