Fana: At a Speed of Life!

ፊንላንድ ኔቶን ለመቀላቀል ወሰነች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መቀላቀል እንደምትፈልግ በይፋ አስታወቀች።

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ ከካቢኔያቸው ጋር በነበራቸው ስብሰባ፥ ፊንላንድ የኔቶ አባል ለመሆን በምታቀርበው የአባልነት ጥያቄ ላይ ተስማምተዋል።

የመንግስት ካቢኔ መስማማቱን ተከትሎ የአባልነት ጥያቄው ለመጽደቅ የፓርላማ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል።

ውሳኔውን ታሪካዊ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ዋናው ነገር የፊንላንድና የህዝቦቿ ደህንነት መሆኑን ገልጸዋል።

አያይዘውም ውሳኔው የኖርዲክ አካባቢ ሃገራትን ፀጥታና ትብብር ያጠናክራል ሲሉም ተናግረዋል።

የሃገሪቱ ፓርላማም የአባልነት ጥያቄውን ያጸድቀዋል ብለው እንደሚጠብቁ መግለጻቸውን አር ቲ ዘግቧል።

የፊንላንድ አባል የመሆን ፍላጎት በፓርላማው ከጸደቀ የኒኒስቶ አስተዳደር ይፋዊ ጥያቄውን ለኔቶ የሚያቀርብ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.