Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን 4 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን 4 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግቦች ሙጅብ ቃሲም በፍፁም ቅጣት ምት 48ኛና 74ኛ ደቂቃዎች ፣ ይሁን እንደሻው በ72ኛው ደቂቃ እና ናትናኤል ወ/ጊዮርጊስ 85ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል።

አዳማ ከተማዎች ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።

በዚህም ፋሲል ከነማ ፕሪሚየር ሊጉን በ19 ነጥብ እየመራ ይገኛል።

አዳማ ከተማ 7 ጨዋታዎችን አድርጎ በ7 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ጊርጌ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ጎል በማስቆጠር ሙጂብ ቃሲም በ11 ፣አቡበከር ናስር በ8 እና ጌታነህ ከበደ በ7 ግቦች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ እየመሩ ይገኛሉ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.