Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ተረከበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

በዚህም አዳማ ከተማን በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የፋሲል ከነማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ በዛብህ መለዮ 12ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎም ፋሲል ከነማ በ29 ነጥብ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት መረከብ ችሏል።

በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ቡና እና ስሑል ሽረ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባካሄዱት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና 6 ለ l በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች አቡበከር ናስር፣ ሃብታሙ ታደሰ እና ሚኪያስ መኮንን አስቆጥረዋል።

የስሑል ሽረን ብቸኛ ግብ ደግሞ ሀብታሙ ሸዋለም አስቆጥሯል።

ፕሪሚር ሊጉን ፋሲል ከነማ በ29 ነጥብ ሲመራ አንድ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የቀራቸው ቅዱስ ጊየርጊስ እና መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ጠቀምጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.