Fana: At a Speed of Life!

ፌስቡክ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ፌስቡክ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት ጠንካራ ቁጥጥር እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ።

የፌስቡክ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ በጀርመን ሙኒክ የፀጥታ ጉባኤ ላይ፥ በተለይም በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሃሰተኛ መረጃወች ላይ ቁጥጥር ያስፈልጋል ብለዋል።

ሃገራትም የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት ጠንካራና ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርጉ ይገባልም ነው ያሉት።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የቴሌኮምና የሚዲያ ኩባንያዎችን ያካተተ አዲስ አሰራር ሊኖር እንደሚገባም ሃሳብ አቅርበዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ፌስ ቡክ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከዚህ ጋር ተያይዞ በየቀኑ ከ1 ሚሊየን በላይ ሃሰተኛ የፌስ ቡክ አድራሻዎች እንደሚዘጉም ገልጸዋል።

ፌስ ቡክ በገጹ ላይ በሚተላለፉ የፖለቲካ ይዘት ባላቸው ማስታወቂያዎች ላይ በሚከተለው ፖሊሲ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል።

ኩባንያው ከዚህ ቀደም የተከፈለባቸው የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን በገጹ ላይ እንዲተላለፉ በማድረግ፥ የማስታወቂያዎቹ ቅጅዎች ለተጠቃሚዎች በሚታይ መልኩ ለሰባት አመታት በመረጃ ቋቱ እንዲከማቹ ያደርግ ነበር።

ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ግን ይህ አሰራር ይቀራል ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.