Fana: At a Speed of Life!

ፌዴሬሽኑ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከውድድር አገደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከማንኛውም ውድድር ማገዱን አስታወቀ።

ፌዴሬሽኑ ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በጻፈው ደብዳቤ፥ ባለፈው ዓመት ክለቡን ካገለገሉት ስምንት ተጫዋቾች ጋር በተያያዘ ጥር 14 ቀን 2012 ዓ.ም በፍትህ አካላት በ10 ቀናት ውስጥ ውሳኔውን እንዲተገብሩ የጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸው እንደነበር አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ወልዋሎዎች በሚመለከተው የፍትህ አካል የተላለፈውን ውሳኔ በተሰጣቸው ጊዜ መሰረት አለመፈጸማቸውን ገልጿል።

ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቡ ፌዴሬሽኑ ከሚሰጣቸው ማናቸውም አገልግሎቶች መታገዱንም ነው ያስታወቀው።

ምንጭ፥ ሶከር ኢትዮጵያ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.