Fana: At a Speed of Life!

ፍላጎትና ጥረት ካለ ሰላምና መረጋጋትን መፍጠር እንደሚቻል የሶማሌ ክልል ማሳያ ነው – የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍላጎትና ጥረት ካለ ሰላምንና መረጋጋትን መፍጠር እንደሚቻል የሶማሌ ክልል ማሳያ መሆኑን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ።

የፌደራል፣ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሰላም ዘርፍ የጋራ ምክክር መድረክ በጅግጅጋ ተጀምሯል።

“የሰላም ቤተሰብ እርስዎ ነዎት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የውይይት መድረክ ላይ የሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የፌደራል የክልልና የከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ አካላት አመራሮችና ባለድርሻዎች ታሳታፊ ናቸው።

የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፣ በሶማሌ ክልል ባለፉት ሁለት አመት ተኩል የነበረውን አሰራር በመቀየር እና ሰላም በማስፈን የለውጡ አካል የሰራው ስራ ፍላጎትና ጥረት ካለ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።

የውይይት መድረኩም የጥናት ውጤቶችን መሰረት በማድረግ ለመማማር ፣ ስራዎችን በቅንጅት ለመተግበርም ያግዛል ማለታቸውንም ኢብኮ ዘግቧል፡፡

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በበኩላቸው እውነተኛ ሰላምን በጦርና በጠብመንጃ ማስፈን እንደማይቻል ያለፈው ስርዓት ማሳያ ነሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የቀደመው ስርዓት የቀበረው የክፋት ፈንጂ በየጊዜው እየፈነዳ ሰላም እንዳያሳጣን ተግቶ መስራት ይገባልም ነው ያሉት።

ለዚህም ኢትዮጵያውያን ያላቸውን የዳበረ አብሮ የመኖር ልምድ ወደ ፖለቲከኞች እና ምሁራን በማምጣት ማዳበር እና መተግበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.