Fana: At a Speed of Life!

ፍልሰትን ለማስተዳደር እየተከናወነ ስላለው ስራና የቀጣይ ስራ አቅጣጫን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍልሰትን ከማስተዳደር አንጻር እየተከናወነ ስላለው ስራና የቀጣይ ስራ አቅጣጫን መሰረት ያደረገ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የብሔራዊ ትብብር ጥምረት ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት በሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ለስራ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀሎችን በተመለከተ ስለተከናወኑ ተግባራት ለባለድርሻ አካላት ሪፖርት አቅርቧል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ፈቲያ ሰይድ ውይይቱ እየተከናወኑ ያሉ ሰራዎችን ከማሳወቅም ባሻገር ለቀጣይ ስራ ግብዓት የሚሆን ሀሳብ ለማሰባሰብና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ከህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር የመቅረፍና የተሻለ ስራ የመስራት አላማን ያነገበ ውይይት ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በጽህፈት ቤቱ ከተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት መካከል ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ምንነትና አስከፊነትን በተመለከተ፣ ከስደት ተመላሽና ተጎጂዎችን ማቋቋምና ድጋፍ ማድረግ እና ህግን ከማስከበር ረገድ መደረግ ስላለበት ሂደት በየደረጃው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ተከናውኗል ብለዋል ሃላፊዋ፡፡

በዚህም በማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ሪፖርት ለቤቱ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመጨረሻም ለቀጣይ ስራ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችና አስተያየቶች የተሰባሰቡ ሲሆን በቋሚነት እየተገናኙ ውጤት አምጪ ስራ ለመስራት የሚያስችል የግንኙነት መደላድል መዘርጋቱን ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.