Fana: At a Speed of Life!

ፍራንክ ላምፓርድ ከቼልሲ አሰልጣኝነት ተሰናበተ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ፍራንክ ላፓርድ ከቼልሲ መሰናበቱን ቡድኑ አስታወቀ።

የቼልሲ ኮኮብ ተጫዋች የነበረው እና ቡድን ማውሪዚዮ ሳሪ የተረከበው ፍራንክ ላምፓርድ ከሃምሌ ወር 2019 ጀምሮ ክለቡን በአሰልጣኝነት ሲመራ ነበር።

ክለቡ ባወጣው መግለጫ ውሳኔው በጣም ከባድ ነው ማንም ይህ ውሳኔ በቀላሉ አይወስደውም ብሏል።

ፍራንክ ላምፓርድ ከቡድኑ ጋር ላስመዘገበው ስኬታ ምስጋና አለን ያለው ቼልሲ ነገር ግን በቅርብ ጊዜያት የክለቡ ውጤት እና አቅም ከሚጠበቀው በታች ሆኗል ብሏል በመግለጫው።

ክለቡን ላለፉት 18 ወራት በአሰልጣኝነት የመራው ላምፓርድ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች አምስቱን መሸነፉን ተከትሎ ነው ስንብቱ የተሰማው።

ባለፈው የውድድር ዘመን አራተኛ ደረጃን በመያዝ ቼልሲ እንዲያጠናቀቅ ማስችላሉ በስኬት ይነሳለታል።

በዘንድሮው የዝውውር ዘመን 275 ሚሊየን ዶላር ክለቡ ወጪ ቢያደርግም በፕሪሚየር ሊጉ እያስመዘገበ የሚገኘው ውጤት አመርቂ አለመሆኑ ለላምፓርድ ስንብት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ጎል ዘግቧል።

ቼልሲ በፕሪሚየር ሊጉ በ29 ነጥብ 9ነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.