Fana: At a Speed of Life!

“ፓራሳይት” የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ ፊልም የ2020 ኦስካር ሽልማት አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012(ኤፍ.ቢ .ሲ) “ፓራሳይት” የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ ፊልም በዘንድሮው የኦስካር ሽልማት በምርጥ ፊልም ዘርፍ አሸንፏል።

92ኛው የኦስካር ሽልማት ስነ ስረዓት በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ ሎስአንጀለስ ከተማ ተካሂዷል።

በስነ ስርዓቱ ላይ “ፓራሳይት” የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ ፊልም በዘንድሮው የኦስካር ሽልማት በምርጥ ፊልም ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።

ፊልሙ በደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሴኡል በሚኖሩ እና በተለያየ የኢኮኖሚ ደረጃ በሚገኙ ሁለት ቤተሰቦች የህይወት ውጣ ውረድ ዙሪያ የሚያጠነጥን መሆኑ ተነግሯል።

በኦስካር ሽልማት ታሪክ በእግሊዝኛ ቋንቋ ያልተሰራ ፊልም በምርጥ ፊልም ዘርፍ ሲያሸንፍ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ይህን ተከትሎ ታሪካዊ ፊልም ለመባል የበቃው “ፓራሳይት” በአጠቃላይ በአራት ዘርፎች የኦስካር ሽልማቶችን መቀዳጀት ችሏል።

የፓራሳይት ፊልም ዳይሬክተር ቦንግ ጁን ሆ ቢት በኦስካር የዓመቱ ምርጥ ዳይሬክተር ዘርፍ ተሸልሟል።

በሌላ በኩል ሬኔ ዜልዌገር “ጁዲ” በተሰኘው ፊልም የጁዲ ጋርላንድን ገጸ ባህርይ በመወከል በምርጥ የሴት ተዋናይ ዘርፍ አሸናፊ ሆናለች።

ጆዋኩን ፊኒክስ ደግሞ “ጆከር” በተሰኘው ፊልም በወንዶች ምርጥ ተዋናይ ዘርፍ የኦስካር ሽልማት አሸናፊ መሆን ችሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.