Fana: At a Speed of Life!

ፓርላማው አሸባሪው ሸኔ በምዕራብ ወለጋ እና በሌሎች አካባቢዎች በንጹሐን ዜጐች ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ በጽኑ አወገዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ እና በሌሎች አካባቢዎችም በአሸባሪው ሸኔ እና ሌሎች መሰል ተላላኪ ጽንፈኛ ኃይሎች አማካኝነት፣ በንጹሐን ዜጐች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በጽኑ አውግዟል፡፡

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአገሪቱን ፀጥታ ከሚመሩ እና ከምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በስፋት ተወያይቷል፡፡

በውይይቱም ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ እና በሌሎች አካባቢዎችም በአሸባሪው ሸኔ እና ሌሎች መሰል ተላላኪ ጽንፈኛ ኃይሎች አማካኝነት፣ በንጹሐን ዜጐች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በጽኑ አውግዟል፡፡

በአንጻሩ መንግስት የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥልም በአጽንዖት አሳስቧል፡፡

በቅርቡ በተለያዩ የሀገራችን ስፍራዎች ማለትም በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ እና በሌሎችም አካባቢዎች ዜጎች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተመላክቷል፡፡

ከሞት የተረፉትም ተፈናቅለው ለአካል እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ተዳርገዋል ሀብት ንብረትም ወድሟል ያለው ምክር ቤቱ፥ ይህንን ዕኩይ ተግባር ምክር ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም የምክር ቤቱ አባላት የየራሳቸውን ድርሻ እንደሚወጡ በምክክር መድረኩ አረጋግጠዋል፡፡

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቀጣይ ትኩረት በሚፈልጉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆነው ችግሩን ለመፍታት እንደሚሠሩ ገልጸው÷በአሁኑ ጊዜ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በአንድነት ቆመን መሻገር አለብን ብለዋል፡፡

ለሕዝባችን ሕልውና ቀን እና ማታ ከሚለፉ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የሚሠሩ ተግባራትን በተመለከተም፥ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ከሌሎች የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በቁርጠኝነት ለመንቀሳቀስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከውስጥ እና ከውጭ ኃይሎች የተጋረጠብንን የሕልውና ጥያቄ ለመመለስ በመንግስት በኩል የተያዘውን የለውጥ መንገድ ማገዝ እንደሚገባም አስምረውበታል።

ለተግባራዊነቱም በትጋት እንደሚረባረቡ የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከምርክ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.