Fana: At a Speed of Life!

ፓርቲዎች ውጤት በቦርዱ እስከሚገለፅ መግለጫ ከመስጠት እንዲታቀቡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓርቲዎች የድምፅ መስጠት ሂደት እና ቆጠራ ተጠናቆ በቦርዱ ውጤት እስከሚገለፅ ድረስ መግለጫ ከመስጠት እንዲታቀቡ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት አሳሰበ።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ዶክተር ራሄል ባፌ ፓርቲዎች የድምፅ መስጠት ሂደት እና ቆጠራ ተጠናቆ፣ በቦርዱ ውጤት እስከሚገለፅ መግለጫ ከመስጠት እንዲታቀቡ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ቦርዱ ከፓርቲዎች እየቀረቡ ላሉ ቅሬታዎች ተገቢና ወቅታዊ እንዲሁም አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት ሂደቱን ማጠናከር አለበት ብለዋል።

ምክር ቤቱ መንግስት የህዝብን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጡን ስራ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቆ ህዝቡም ለሰላሙ ቅድሚያ በመስጠት በአንድነት እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.