Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።

ፕሬዚዳንቷ ለታንዛኒያ ሕዝብና መንግስት፣ ለፕሬዚዳንቱ ቤተሰቦችና ለምክትል ፕሬዚዳንቷ ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን በራሳቸው፣ በኢትዮጵያ ሕዝብና በመንግስት ስም በፕሬዚዳንቱ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክትም ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ለአገራቸው እድገትና ሠላም ለማምጣት ባደረጉት ጥረት ሲታወሱ እንደሚኖሩ ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በተጨማሪም በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ምክትል ፕሬዚዳንቷ የተጣለባቸውን ከፍተኛ ሀላፊነት በብቃት እንደሚወጡ ያላቸውን መልካም ምኞትና ድጋፍ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከስድስት ሣምንታት በፊት በታንዛኒያ በነበራቸው የስራ ጉብኝት ከፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች የተወያዩ የመጨረሻዋ ርዕሰ ብሔር መሆናቸውን ከፕሬዚዳንቷ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.