Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በአልጀሪያ 60ኛ ዓመት የነጻነት ቀን ክብረ በዓል ላይ ለመታደም አልጀርስ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአልጀሪያ 60ኛ ዓመት የነጻነት ቀን ክብረ በዓል ላይ ለመገኘትና ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አልጀርስ ከተማ ገብተዋል።
 
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአልጀሪያ አቻቸው ፕሬዚዳንት አብዱልመጅድ ተቡን በአገሪቱ 60ኛ ዓመት የነጻነት ቀን ክብረ በዓል ላይ እንዲታደሙ በላኩላቸው ግብዣ መሠረት ነው ወደ አልጀርስ ያቀኑት፡፡
 
ፕሬዚዳንቷ በአልጀሪያ ቆይታቸውም ከፕሬዚዳንት ተቡን ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የረጅም ጊዜ ግንኙነት በላቀ ሁኔታ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አልጀሪያ በፈረንጆቹ ከ1830 ጀምሮ የፈረንሣይ ቅኝት ግዛት የነበረች ሲሆን÷ በፈረንጆች ሐምሌ 5 ቀን 1962 ከረጅም ዓመታት የትጥቅ ትግልና ከፍተኛ መስዋዕትነት በኋላ ነጻነቷን ለመቀናጀት ችላለች።
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.