Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ደቡብ አፍሪካ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ አፍሪካ ገቡ።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጆሐንስበርግ ኦሊቨር ታምቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ አፍሪካ የማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ሊንዲዌ ዙሉና በደቡብ አፍሪካ የኢፌዴሪ መንግስት ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በደቡባዊ አፍሪካ የተመድ አስተባባሪና ተቀማጭ ናርዶስ በቀለ ቶማሰ፣ የፕሪቶሪያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ባልደረቦችና በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አመራሮችም በአቀባበሉ ላይ ተገኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በደቡብ አፍሪካ ቆይታቸው ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.