Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ኻሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ኤምባሲ ተገኝተው ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቷ በኤምባሲው በተዘጋጀው የኀዘን መግለጫ መዝገብ ላይ ፥ “በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሼክ ኻሊፋ ቢን ዛይድ አል ናሀያን ኅልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ኀዘን በራሴ እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ለመግለጽ እወዳለሁ” የሚል መልዕክት አስፍረዋል።

ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ሕዝብ እና መንግሥት፣ ለአዲሱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እንዲሁም ለንጉሣውያን ቤተሰቡም መፅናናትን ተመኝተዋል።

ኢትዮጵያ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ጋር ያላትንን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥልም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በኀዘን መግለጫቸው ላይ ማስፈራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ከአውሮፓውያኑ 2004 ጀምሮ የተባበሩት ዓረብ ኢማሬቶችን የመሩት ሼክ ኻሊፋ ቢን ዛይድ አል ናሀያን በ73 ዓመት ዕድሜያቸው ሕይወታቸው አልፏል።

እርሳቸውን ተክተው ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናሀያን የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.