Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ “የኢትዮጵያ እናቶች የሰላም ጥሪ” አባላትን አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከተለያዩ የሃይማኖት እና ሌሎች ተቋማት የተውጣጡ “የኢትዮጵያ እናቶች የሰላም ጥሪ” አባላትን በጽሕፈት ቤታቸው አነጋገሩ።
“የኢትዮጵያ እናቶች የሰላም ጥሪ” አባላት ላለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ለዘለቀው የሰላም እጦት እናታዊ መፍትሔ ለማፈላለግ እንደሚሠሩ አስረድተው÷ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ለዚህ ጥሪ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ከተለያዩ የህብረተሰብ እና የሙያ ዘርፎች ተውጣጥታችሁ ለአገራችን ሰላምና እድገት አስተዋጽዖ ለማድረግ በመነሳሳታችሁ ልትመሰገኑና ልትደገፉ ይገባል ብለዋል፡፡
አያይዘውም÷ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በተመሳሳይ ሁኔታ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.