Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ የዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርዓት የወደፊት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርዓት የወደፊት ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለማቀድ ከተቋቋመው ኮሚሽን ጋር ተወያዩ፡፡

ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምሁራንንና ባለሙያዎችን ያቀፈው ነው ተብሏል፡፡

ለወደፊት ዘመናዊ እና ሁሉን አቀፍ ትምህርት ምን መምሰል እንዳለበት ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለመምህራንና ለተማሪዎች መመሪያ ሆኖ የሚያገለግል ሪፖርት እያዘጋጀ ነው፡፡

ኮሚሽኑ እስካሁን የተሠራውን ሥራና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙ አስተያየቶች ላይ በሰፊው መወያየታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኮሚሽኑ በፈረንጆቹ በ2019 በኒውዮርክ በተካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ተጓዳኝ መመስረቱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.