Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ለግብጹ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ ኤል ሲሲ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በራሳቸው እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ስም ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት፥ የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረከ ለሀገራቸው እድገት ብዙ የሰሩ መሆናቸውን አውስተዋል።

ለግብጽ ህዝብ እና መንግስት እንዲሁም ለቀድሞው ፕሬዚዳንት ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶችም መፅናናትን ተመኝተዋል።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ነው፣

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.