Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በኢትዮጵያ የተሾሙ የሰባት ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የተሾሙ የሰባት ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ መቀበላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሹመት ደብዳቤዎችን ያቀረቡ አምባሳደሮች በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሮበርት ሼትኪንቶንግ ፣ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢሂዩዋን፣ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሾዛብ አባስ ፣ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካንግ ሴኦሄ፣ በኢትዮጵያ የቱኒዚያ አምባሳደር አብዱልሀሚድ ግሃርቢ እና በኢትዮጵያ የዚምባብዌ አምባሳደር ታኦንጋ ሙሰሃያቫንሁ ናቸው።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙት አጠናክራ ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።
የሹመት ደብዳቤውን ካቀረቡት ከተወሰኑት ሀገራት ጋር በተፈጠረ ስትራቴጂካዊ ትብብር የተገኘውን ጥቅም በማብራራት ሌሎች ሀገራትም ይህንኑ መንገድ እንደሚከተሉ ተስፋቸውን ገልፀዋል።
ፕሬዚዳንቷ ለአምባሳደሮቹ መንግስት በትግራይ ክልል ያካሄደውን ህግን የማስከበር ዘመቻ ካጠናቀቀ በኋላ እያከናወነ ስላለው መልሶ የማቋቋም ስራ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አምባሳደሮቹ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ያከናወነችውን ዘመቻ በስኬት በማጠናቀቋ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
እንዲሁም በኢትዮጵያና በወከሏቸው ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ያላቸው ቁርጠኝነት ገልፀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.