Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በጁቡቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ንግግር አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጅቡቲ ብሄራዊ ምክር ቤት በመገኘት ንግግር አድርገዋል።
በምክር ቤቱ በክብር እንግድነት የተገኙት ፕሬዚዳንቷ በደም፣ ባህል ፣ ሀይማኖት እና ቋንቋ ጥልቅ ግንኙት ስላላቸው የሁለቱ ሀገራት የተለየ ግንኙነት ገለፃ አድርገዋል።
ይህን ትልቅ እድል ለኢኮኖሚያዊ ውህደት ለመጠቀም መስራት እንደሚያስፈልግ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጥሪ አቅርበዋል።
የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት መሀመድ አሊ ሆሜድ በበኩላቸው ሀገራቸው ሰላምን ለማስቀጠል እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጎን ለመሆን ሰዓት አታባክንም ብለዋል።
በዚህ ስብሰባ ላይ የምክር ቤቱ አባላት፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች እና ከፍተኛ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
 
በዚህ ወቅት ዋና ፃሃፊው ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ፣ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ አሊ የሱፍ እና የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ተገኝተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.