Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢስሌይ ጋር ተወያዩ፡፡

ዋና ዳይሬክተር ድርጅታቸው በኢትዮጵያ እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በበኩላቸዉ ድርጅቱ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ እየሰራ ያለዉን እንቅስቃሴ አበረታተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለአፍሪካ እያከፋፈለ ላለው የኮቪድ 19 መከላከያ ቁሳቁስ እንደ መነሻና እንደ ማከማቻ መመረጧን የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታውሷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተሩ ዛሬ ረፋድ ላይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.