Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከፊንላንዱ ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
በትናንትናው እለት በስልክ በነበራቸው ቆይታም በወቅታዊ የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ እንዲሁም በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የፊንላንድ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትግራይ ክልል ስለተካሄደው ህግን የማስከበር ዘመቻ እንዲሁም በዘመቻው ምክንያት ለተፈናለቀሉ ዜጎች እየተደረገ ስላለው ድጋፍ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እና የፊንላንዱ ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይም የተወያዩ ሲሆን፥ በተለይም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ መምከራቸውም ተገልጿል።
ሁለቱም ፕሬዚዳንቶች በኢትዮጵያ እና በፊንላንድ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውም ታውቋል።
ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ በትዊተር ገፃቸው ላይ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ እና ፊንላንድ ሁለትዮች ትብብር ዙሪያ ስላደረጉት ውይይት ምስጋናቸውን ገልፀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.