Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የዓለም አቀፍ የክትባት ጉባኤ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የዓለም አቀፍ የክትባት ጉባኤ ላይ ተሳተፉ፡፡

ፕሬዚዳንቷ በጉባኤው ባደረጉን ንግግር ኮቪድ-19 ን ለመቆጣጠር ለሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት የጉባኤው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል ፡፡

ከ20 ዓመት በፊት ከ30 በመቶ በታች የነበረው በኢትዮጵያ የክትባት ሽፋን መንግሥት በሰጠው ትኩረትና በአጋሮች ድጋፍ 72 በመቶ መድረሱን ለክትባት የሚመደበው ከጤናው ዘርፍ በጀት 40 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል::

በሀገሪቱ አነስተኛ ሽፋን የሚታባይባቸውን አካባቢዎች በመለየትም የክትባት ሽፋኑን የሚፈለግበት ደረጃ ለማድረስ መንግስት የያዘውን ከፍተኛ ቁርጠኝነት አብራርተዋል፡፡

ዓለም በኮቪድ-19 የተነሳ ለገጠማት ችግር መፍትሔ ፍለጋችን ከውድድር ይልቅ ትብብርን ማስቀደም እንደሚገባና የክትባቱ ሥርጭት ደሃና ሃብታም አገሮችን መለየት እንደሌለበት አሳስበዋል::

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጠሩት ዓለም አቀፍ የክትባት ጉባኤ የበርካታ ሀገራትና መንግሥታት መሪዎች መሳተፋቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.