Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ የሕዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት በመጀመሩ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን ዛሬ ኃይል ማመንጨት በመጀመሩ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ፕሬዚዳንቷ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የግድቡ 2ኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት በመጀመሩ የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንኳን ደስ አለን ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ዩኒት 9 በዛሬው እለት ሃይል ማመንጨት ጀምሯል።
ግድቡ ካሉት 13 ተርባይኖች አንደኛው የሆነው የዩኒት 9 ተርባይን አሁን ባለው የግድቡ ከፍታ እና በያዘው የውሃ መጠን 270 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል አለው።
ግድቡ በሙሉ አቅም ወደ ስራ ሲገባ ተርባይኑ 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.