Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት አላሳኔ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአይቮሪኮስቱ ፕሬዚዳንት አላሳኔ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከፓርቲያቸው በረቀረበላቸው ጥሪ መሰረት በመጭው ጥቅምት ወር በፕሬዚዳንትነት እንደሚዳደሩ ተናግረዋል፡፡

ሃገራቸውን ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ በፕሬዚዳንትነት እየመሩ የሚገኙት ኦታራ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በድጋሚ እንደማይወዳደሩ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጅ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አማዱ ኩሊባሊ ባለፈው ወር ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ ፓርቲያቸውን ወክለው እንዲወዳደሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል ተብሏል፡፡

ይህን ተከትሎም የፓርቲውን ጥሪ በመቀበል በመጭው ምርጫ እውዳደራለሁ ብለዋል፡፡

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው ኦታራ ህገ መንግስቱን እንዲያከብሩ ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በአንጻሩ ሁለት ጊዜ ሃገራቸውን የመሩበት የስልጣን ጊዜ በፈረንጆቹ 2016 ድጋሚ በተከለሰው የሃገሪቱ ህገ መንግስት አይቆጠርም በማለት መወዳደር እችላለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ተፎካካሪዎቻቸውም ሃገሪቱ ዴሞክራሲን ታስቀጥል እያሉ ነው፡፡

ምንጭ፣ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.